በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያና የኤርትራ የሰሞኑ ፖለቲካ


የኢትዮጵያና የኤርትራ የሰሞኑ ፖለቲካ
የኢትዮጵያና የኤርትራ የሰሞኑ ፖለቲካ

አቶ ነአምን ዘለቀ በኢትዮጵያና በኤርትራ ያለውን የሰሞኑን ፖለቲካ አስመልክተው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ የመንግሥታቸው ደጋፊ ለሆነ አንድ ዌብ ሳይት በሰጡት ቃለ ምልልስ ኢትዮጵያን ለማተራመስ የሚሹ ተቃዋሚዎችን ትደግፋለች ሲሉ ለገለጿት ኤርትራ አዲስ ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል።

ኤርትራ ኢትዮጵያን ለማጥቃት ከሞከረች “ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የማያዳግም ሥራ ሠርተን እንወጣለን” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስጠንቀቂያ ላይ ኤርትራ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱት ኢትዮጵያዊያን ተቃዋሚዎች አንዱ የሆነው የአርበኞች ግንቦት 7 የዓለም አቀፍ አመራር የውጭ ግንኙነት ኃላፊና የንቅናቄው የምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ነአምን ዘለቀ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛቻ “ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት የሚሠነዘር የተለመደ ፉከራ ነው” ሲሉ አቶ ነአምን ገልፀው “ትግሉ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል አይደለም፤ ትግሉ የኤርትራ መንግሥት ወይም የኤርትራ ሕዝብ አይደለም፤ ትግሉ ነፃነታቸውን፣ መብቶቻቸውን በተነጠቁ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ዜጎችና በዘረኝነት በታወሩ፣ በዘረፋና በሙሰኝነት በደለቡ፣ የትግራይን ሕዝብ በማይወክሉ ጥቂቶች መካከል ነው” ብለዋል።

በቅርቡ የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ሞላ አስገዶም ባለፈው ሣምንት የተወሰኑ ወታደሮችን ይዘው ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ይታወቃል።

አቶ ሞላ ከአንድ ዓመት በላይ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ሲሠሩ መቆየታቸውን ገልፀው ኤርትራ ውስጥ በአራት የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ድርጅቶች የተመሠረተውን “አገር አድን ንቅናቄ” ትተው እንደተመለሱ ይታወቃል።

ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ስለነበራቸው ግንኙነትና አቶ ሞላ የድርጅቱን ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋንና የኤርትራውን ፕሬዚደንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂን በተመለከተ ስላነሷቸው ነጥቦች አቶ ነአምን ዘለቀ የሰጡትን መልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የኢትዮጵያና የኤርትራ የሰሞኑ ፖለቲካ 17'41"
please wait

No media source currently available

0:00 0:17:41 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG