በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሰሜን ኢትዮጵያ የሱዳን እና የኤርትራ ፍልሰተኞች መጠለያቸውን ለቀው ወጡ


ኤርትራና ኢትዮጵያ
ኤርትራና ኢትዮጵያ

በሰሜን ኢትዮጵያ አንድ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሚተዳደር የፍልሰተኞች መጠለያ የነበሩ 1ሺሕ የሚሆኑ የሱዳን እና የኤርትራ ፍልሰተኞች ለቀው መውጣታቸውን ድርጅቱ ዛሬ ዓርብ አስታውቋል።

ፍልሰተኞቹ መጠለያውን ለቀው የወጡት፣ ዝርፊያ ተኩስ እንዲሁም እገታዎች ተፈጽመዋል የሚሉ ሪፖርቶችን ተከትሎ እንደሆነ አንድ የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ባለሥልጣን ለኤ.ኤፍ.ፒ ዜና ወኪል አስታውቀዋል።

በአማራ ክልል በሚገኘው አውላላ የፍልሰተኞች መጠለያ ጣቢያ የነበሩትና ከሱዳን እና ከኤርትራ የመጡት ፍልሰተኞች “ደህንነት ስለማይሰማቸው” ለቀው ወጥተዋል ሲል ተመድ አስታውቋል።

የአውላላ መጠለያ ከመተማ 70 ኪሜ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ የስደተኞች ድርጅቱ እና የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ፍልሰተኞቹ ወደ መጠለያው እንዲመለሱ ቢያበረታቱም፣ ፍልሰተኞቹ አልተቀበሉም። ከመጠለያው 1.5 ርቀው በመንገድ ላይ እንደሚገኙም ታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG