በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ በፕሬስ ነጻነትና በተቃዋሚዎች ላይ የሚደርገው ጫና እንደሚያሳስባት ዩናይትድ ስቴትስ አስታወቀች


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አርማ
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አርማ

"የንግግር ነጻነትን በማረጋግጥና ዲሞክራሲያዊ እርምጃዎችን በማጎልበት የኢትዮጵያ መንግስት ቀደም ሲል የወሰዳቸውን አዎንታዊ እርምጃዎች እንዲያጠናክ እያሳሰብን፤ በነጻ ድምጾች ላይ የሚፈጸመው አፈና ይህን መሰሉን አዎንታዊ እርምጃ ማደናቀፍ ብቻ ሳይሆን፤ የልማትና የምጣኔ ሃብት እድገትንም የሚገታ መሆኑን መጠቆም እንፈልጋለን።” የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር።

በኢትዮጵያ በፕሬስ ነጻነት ላይ የሚደረገው ገደብና የጸረ ሽብር ሕጉን በመጠቀም መንግስት በጋዜጠኞች፥በመብት ተሟጋቾችና በተቃዋሚዎች ላይ የሚያደርገው ጫና የሚያሳስባት መሆኑን ዩናይትድ ስቴትስ አስታወቀች።

በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞው የጋምቤላ አስተዳዳሪ እንዲለቀቁና በኢትዮጵያ የዜጎች መሠረታዊ መብቶችእንዲከበሩ በመጠየቅ አምስት የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት ከትላንት በስቲያ ለፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማየጻፉትን ደብዳቤ ተንተርሶ ለቀረቡ ጥያቄዎች በሰጠው ምላሽ ነው፤ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ይህንያለው።

በሌላ ተያያዥ ዜና፤ የኢትዮጵያ መንግስት በኦሮምያ ክልል በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የወሰደው የኃይል ዕርምጃአሳስቦናል፤ ሲሉ አንዲት የመካከለኛው ምዕራብ ዩናይትድ ስቴትሷ የሜነሶታ ክፍለ ግዛት የምክር ቤት አባል ለግዛቲቱሸንጎ ባቀረቡት ረቂቅ አመልክተዋል።

በኢትዮጵያ በፕሬስ ነጻነትና በተቃዋሚዎች ላይ የሚደርገው ጫና እንደሚያሳስባት ዩናይትድ ስቴትስ አስታወቀች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:03 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG