በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ሱዳን የአማጽያን መሪ የክፍላተ-ሀገር ዕቅዱን ለአፍሪካ ህብረት ለማቅረብ ወስነዋል


ፋይል ፎቶ - የደቡብ ሱዳን ፕረዚዳንት ሳልቫ ኪር በጁባ ቤተ መንግሥት ንግግር እያሰሙ እአአ 2015
ፋይል ፎቶ - የደቡብ ሱዳን ፕረዚዳንት ሳልቫ ኪር በጁባ ቤተ መንግሥት ንግግር እያሰሙ እአአ 2015

የደቡብ ሱዳን የአማጽያን መሪ ሪያክ ማቻር የ28 ከፍላተ-ሀገር ዕቅድ በመቃወም ጉዳያቸውን ለአፍሪካ ህብረት ለማቅረብ ወስነዋል።

የደቡብ ሱዳን የአማጽያን መሪ ሪያክ ማቻር ፕረዚዳንት ሳልቫ ኪር በሀገሪቱ 28 ክፍላተ-ሀገር እንዲኖሩ ለማደረግ ማቀዳቸውን በመቃወም ጉዳያቸውን ለአፍሪካ ህብረት ለማቅረብ ወስነዋል።

የተቃዋሚው ቡድን የሱዳን ህዝባዊ ሀርነት ንቅናቄ የውጭ ጉዳይ ሃላፊ ኢዝየል ሎል ጋቶኩት(Ezeliel Lol Gatkuoth) ማቻር ከነገ ጀምሮ እስከ መጪው ቅዳሜ ድረስ በሚቆየው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ላይ ተገኝተው የአፍሪካ መሪዎች ሳልቫ ኪር 28 ክፍላተ-ሀገር ለመመስረት ያለቸውን እቅድ እንዲተው እንዲነግሯቸው ጥሪ አደርጋለሁ ብለዋል።

ሳልቫ ኪር ባለፈው ጥቅምት ወር ባወጡት አዋጅ በሀገሪቱ 28 ክፍላተ-ሀገር እንደተመሰረቱ አስታውቀዋል። በፊት ግን 10 ክፍላተ-ሀገር ናቸው የነበሩት።

ውሳኔው የተደረገው በደቡብ ሱዳን የሽግግር ህገ-መንግስት በመመራት ነው ብለዋል ፕረዚዳንቱ። አላማውም ማዕካላዊ አስተዳደሩን ለማላላት እንደሆነ ሳልቫ ኪር ሲያስረዱ የብሄራዊ መንግስቱን መጠን በመቀነስ ሀብቱ ለገጠሩ ነዋሪ ቀረብ እንዲል ለማደረግ ነው ብለዋል።

የአማጽያኑ መሪዎች ግን ሀገሪቱን በ 28 ክፍላተ-ሀገር መከፋፈሉ የአንድን ጎሳ መሬት ለሌላ ስለሚሰጥ የባሰ ማህበረሰባው ተቃውሞ ያስነሳል ይላሉ። ዘገባውን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

የደቡብ ሱዳን የአማጽያን መሪ ጉዳያቸውን ለአፍሪካ ህብረት ለማቅረብ ወስነዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:46 0:00

XS
SM
MD
LG