በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ሱዳን ድርድር በባሕር ዳር

ባሕር ዳር
ባሕር ዳር

ካለፈው ነኀሴ 22 ጀምሮ ተቋርጦ የቆየው በተለያዩ የደቡብ ሱዳን ወገኖች መካከል ይካሄዳል የተባለ ድርድር ሰኞ - መስከረም 5/2007 ዓ.ም ባሕርዳር ላይ ይጀመራል ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡

የእርዳታ እህል ለመቀበል የተሰለፉ የደቡብ ሱዳን ሴቶች፤ ሚንካማን፣ ሌክ ስቴት፣ ሰኔ 20/2006 ዓ.ም
የእርዳታ እህል ለመቀበል የተሰለፉ የደቡብ ሱዳን ሴቶች፤ ሚንካማን፣ ሌክ ስቴት፣ ሰኔ 20/2006 ዓ.ም

please wait

No media source currently available

0:00 0:06:07 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ካለፈው ነኀሴ 22 ጀምሮ ተቋርጦ የቆየው በተለያዩ የደቡብ ሱዳን ወገኖች መካከል ይካሄዳል የተባለ ድርድር ሰኞ - መስከረም 5/2007 ዓ.ም ባሕርዳር ላይ ይጀመራል ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡

ተደራዳሪዎቹ ኢትዮጵያ የገቡ ሲሆን የድርድሩ እንደተባለው ከተጀመረ ዋናው የመነጋገሪያ ነጥብ የሚሆነው የሽግግር መንግሥት ምሥረታ ጉዳይ እንደሚሆን ተገምቷል፡፡

ደቡብ ሱዳን ና ኢትዮጵያ
ደቡብ ሱዳን ና ኢትዮጵያ

የምሥራቅ አፍሪካ ሃገሮች የጋራ ልማት ባለሥልጣን - ኢጋድ ቀደም ሲል ወገኖቹ የሁለት ዓመት ተኩል ዕድሜ የሚኖረው የሽግግር መንግሥት እንዲመሠርቱ ሰጥቷቸው የነበረው ቀነ-ገደብ ያለውጤት ከተቃጠለ በኋላ የ45 ቀናት ሌላ ቀነ-ገደብ ቆርጦላቸው እንደነበረ ይታወሣል፡፡

ኢጋድ አቅርቦ በነበረው ሃሣብ የአሁኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በሽግግሩ ወቅት በሥልጣናቸው እንዲቀጥሉ፤ ተቃዋሚዎች ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሰይሙና ስዩሙ ጠቅላይ ሚኒስትርም የፕሬዚዳንቱን ይሁንታ ማግኘት እንዲኖርበት የሚጠይቅ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የተቃዋሚዎቹ ዋና ተደራዳሪ ታባን ዴንግ ጋይ እና የደቡብ ሱዳን መንግሥት ዋና ተደራዳሪ ንሂያል ዴንግ ንሂያል
የተቃዋሚዎቹ ዋና ተደራዳሪ ታባን ዴንግ ጋይ እና የደቡብ ሱዳን መንግሥት ዋና ተደራዳሪ ንሂያል ዴንግ ንሂያል

ይህ ሃሣብ አሁን በሃገሪቱ ውስጥ ያለው ሁኔታ እንዲቀጥል የሚያደርግ ነው ሲሉ ተቃዋሚዎቹ ደስተኛ እንዳልሆኑበት የገለፁ ሲሆን የመንግሥቱ ወገን ግን ተስማምቶ ለድርድሩ ዝግጁ መሆኑን ማስታወቁን ባሕርዳር የሚገኙትን የደቡብ ሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስትርና የተደራዳሪዎቹን ቃል አቀባይ ማይክል ማኩዬይን ያነጋገረው እስክንድር ፍሬው ዘግቧል፡፡

ከእስክንድር ጋር የተደረገውን ጥያቄና መልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG