በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአዳማና በሦስት የተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ዛሬም የተቃዉሞ ስልፍ ቀጥሏል


የመጀመርያ ደረጃ አስተማሪ የለቅሶ ሥነ-ሥርአት በተደረገበት ጊዜ የተገኘ ለቀስተኛ በሆሎንኮሚ ከተማ(Holonkom)እአአ 2015[ፋይል ፎቶ - ሮይተርስ/ REUTERS]
የመጀመርያ ደረጃ አስተማሪ የለቅሶ ሥነ-ሥርአት በተደረገበት ጊዜ የተገኘ ለቀስተኛ በሆሎንኮሚ ከተማ(Holonkom)እአአ 2015[ፋይል ፎቶ - ሮይተርስ/ REUTERS]

በአዲስ አበባና ፊኒፊኔ ዙሪያ የተቀናጀ ማስተር ፕላን የተባለዉ ንድፍ ገበሬዎችን ያፈናቅላል ቋንቋና ባህል ያጠፋል በሚል በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች የሚካሄደዉ ተቃዉሞ የታሰሩት ይፈቱ የሚለዉን መፈክር ጨምሮ ዛሬም በአንዳንድ ስፍራዎች ቀጥሏል።

በምእራብ ሃረርጌ የመሳላ ከተማ፣ በዛሬዉ እለት ተማሪዎች ባካሄዱት ተቃዉሞ የኦሮሚያን ገበሬዎች ያፈናቅላል የተባለዉ የአዲስ አበባና የፊንፊኔ ዙሪያ የተቀናጀ ማስተር ፕላን አዉግዘዉ በተቃዉሞ ሳቢያ የታሰሩ ሁሉ እንዲፈቱና የተገደሉ ሰዎች ቤተ ሰቦች ካሳ እንዲከፈሉ ጠይቀዋል። ዛሬ በተካሄደዉ ሰልፍ ላይ ሁለት ተማሪዎች በጸጥታ አስከባሪዎች ፖሊስ ቆስለዉ ወደ ጭሮ ሆስፒታል መወሰዳቸዉና ከሃያ በላይ የሚሆኑ ሌሎች ደግሞ መታሰራቸዉን ይደርስብኛል ያለዉን ጥቃት በመፍራት ስሙ እንዳይገለጥ የጠየቀ ተማሪ ገልጿል። ትላንት ምሽት የዛሬዉን ሰልፍ ለማካሄድ ተማሪዎች የሚያደርጉትን እቅድ የሰሙ ፓሊሶች ማለዳ በመሳላ ከተማ በመሰማራት ያገኙትን ወጣት ደብድበዋል ብሏል።

“ተማሪዎችን ሳይሆን የቀን ሰራተኞን መደብደብ ጀመሩ፣ እነርሱም በመደብደባቸዉ ተቆጥተዉ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን በመቀላቀል በሰልፉ ተካፈሉ" ብለዋል።

በተጨማሪም የወረዳዋ ፓሊሶችና ካቢኔ አባላት ተኩስ ከፍተዉብን እኛም ድንጋይ ወርዉረን ተከላክለናል ብሏል ተማሪዉ፣ ተከሰተ የተባለዉን የተቃዉሞ ስልፍና ጉዳት አስመልክቶ የመሰላ ከተማ ወረዳ አስተዳዳሪና ደህንነት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ዲኔ አህመድን እንዲሁም የምእራብ ሀረርጌሬ ዞን አድተዳዳሪ አቶ አልዩ ኡመሬን በወረዳዉ የኦህዴድ ድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ሙክታርን ለማነጋገር ያደረግነዉ ሙከራ ስልካቸዉ ስለማይነሳ አልተሳካም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ትላንት በአዳማ ዩኒቬርሲቲ ቅጥር ጊቢ ዉስጥ በተካሄደ ተቃዉሞ ሁለት ተማሪዎች በፌዴራል ፖሊሶች መገደላቸዉ ታዉቋል።

አዳማ ዩኒቬርሲቲ
አዳማ ዩኒቬርሲቲ

አንደኛዉ ተማሪ ወዲያው ሲሞት የሁለተኛዉ ሕይወት ያለፈዉ ዛሬ መሆኑን ጥቃት እንዳይደርስበት በመስጋት ስሙን እንዳይጠቀስ የጠየቀ ተማሪ ገልጾልናል።

ተማሪዉ በዩኒቬርሲቲዉ ቅጥር ግቢ ፍርሃት እንደነገሰና ለራሱም ሕይወት እንደሚሰጋ ጨምሮ ገልጾልናል።

ትላንት በፌዴራል ፖሊሶች ተገደሉ ስለተባሉ ተማሪዎች ለማጣራት ወደ አዳማ ፖሊስ ጣቢያ ስልክ ደዉለን ፖሊስ ደረጀ አድነዉን አግኝተናል።

"አዎ የዚህ መስሪያ ቤት አባል ነኝ ፣ ነገር ግን በዚህ ጉዳይ ላይ የተጣራ መረጃ የለኝም ፥ ጠዋት በዩኒቨርሲቲዉ ትንሽ ረብሻ እንደነበር ሰምቻለሁ በተረፈ ሰላም ነዉ" በማለት ለቪኦኤ መልስ ሰጥቷል።

በዩኒቨርስቲዉ ተማሪዎች ያሉበትን ሁኔታ እንዲያስረዱም ወደ አዳማ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚደንት ዶክተር ለሚ ጉታ ቢሮም ስልክ ደዉለን ነበር ስልካቸዉ አይነሳም።

በምስራቅ ወለጋ ጊዳ አያና ከተማ የመሰናዶና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ከዚህ በፊት እንዳደረጉት ሁሉ ጥቁር ልብስ ለብሰዉ ወደ ትምህርት ቤት በመሄድ ተቃዉሞና መፈክሮቻቸዉን አሰምተዉ እንደተመለሱ ከስፍራዉ ያነጋገርናቸዉ የዓይን እማኝ ገልጸዉልናል።

ከጊዳ አያና ከተማ ካሁን በፊት ቁጥጥር ስር የዋሉ ከፊል ተማሪዎች መፈታታቸዉንና ሌሎች ግን አሁንም ታስረዉ እንደሚገኙ እኚሁ የዓይ እማኝ ገልጸዉልናል። በምስራቅ ወለጋ የጊዳ አያና ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ማረጋ ቀነዓ ስልካቸዉን አያነሱም። የወረዳዉ የትምህት ቢሮ ሃላፊ አቶ አዳነ አላምረዉ ስልኩን አንስተዉ የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ክፍል ባልደረባችን ነሞ ዳንዲ ሊያነጋግር እራሱን ሲያስተዋዉቅ ስልኩን ዘግተዉታል።

ሰፋ ያለ ዝርዝር ባለደረባችን ነሞ ዳንዲ ወደ ከተሞቹ ስልክ በመደወል ያጠናቀረዉን ዘገባ ትዝታ በላቸዉ አቅርባዋለች። ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

በአዳማና በሦስት የተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ዛሬም የተቃዉሞ ስልፍ ቀጥሏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:47 0:00


XS
SM
MD
LG