በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማይክሮሶፍት ኢንዶኔዥያ ውስጥ ለልዩ ልዩ ቴክኖጂዎች መሠረተ ልማት 1.7 ቢሊዮን ዶላር ወጭ ሊያደርግ ነው


የማይክሮሶፍት ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳታያ ናዴላ በጃካርታ ንግግር አያደረጉ እአአ ሚያዚያ 30/2024
የማይክሮሶፍት ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳታያ ናዴላ በጃካርታ ንግግር አያደረጉ እአአ ሚያዚያ 30/2024

የማይክሮሶፍት ኩባንያ በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ውስጥ ኢንዶኔዥያ ውስጥ ለሚገነባቸው የሰው ሰራሽ ልህቀት እና የኮምውተር መረጃዎችን በኢንተርኔት አማካኝነት ማከማቸት የሚያስችሉ ቴክኖጂዎች መሠረተ ልማት ግንባታ የሚውል 1.7 ቢሊዮን ዶላር ሊመድብ መሆኑን አስታወቀ። ይህም የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ድሬክተር ሳታያ ናዴላ እንዳመለከቱት ማይክሮሶፍት በዚያች አገር የ29 አመታት ታሪኩ ትልቁ ወጭ ነው።

የሰው ሰራሽ ልሕቀት ቴክኖሎጂን በመተግበር ሥራን ለማቀላጠፍ እና ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የመሪነቱን ሥፍራ ለመቆናጠጥ ጥረት የያዘው ማይክሮሶፍት ካለፈው ጥር እስከ መጋቢት ወር መገባደጂያ የአውሮፓውያኑ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ትርፉ በ20 በመቶ መጨመሩን ባለፈው ሳምንት ይፋ አድርጓል።

ይህ የAI ቴክኖሎጂ ዋና አላማው የምጣኔ ሃብት እድገት እንቅፋቶችን ለመቅረፍ ነው፤ ግባችንም በጋራ በምንሰራቸው ሥራዎች ይህን እንደ አዲስ ግብአት በመውሰድ የኢኮኖሚ እድገትን ማቀላጠፍ መቻል ነው"

"ይህ የAI ቴክኖሎጂ ዋና አላማው የምጣኔ ሃብት እድገት እንቅፋቶችን ለመቅረፍ ነው፤ ግባችንም በጋራ በምንሰራቸው ሥራዎች ይህን እንደ አዲስ ግብአት በመውሰድ የኢኮኖሚ እድገትን ማቀላጠፍ መቻል ነው" ሲሉ ናዴላ የደቡብ ምስራቅ እስያ አገራት ጉብኝታቸው የመጀመሪያ መዳረሻ ካደረጓት ጃካርታ ላይ በሰጡት አስተያየት አመልክተዋል ።ማይክሮሶፍት ደቡብ ምስራቅ እስያን እያደገ የመጣ የቴክኖሎጂው ገበያ እና ለተጨማሪ የኤአይአይ ቴክኖሎጂዎች ግንባታ አመቺ ሥፍራ አድርጎ ይመለከታል። በግዛቱ የሚታየው ከኤአይአይ ቴክኖሎጂ

የተዛመደ እንቅስቃሴም በክልሉ የምጣኔ ሃብት ገጽታ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ይጠበቃል።

በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረገው ይህ ወጭ ለ840, 000 ሰዎች የAI ስልጠና ዕድል የሚያስገኝ እና በኢንዶኔዥያ ቁጥሩ እየጨመረ ለመጣው በቴክኖሎጂው ዘርፍ የተሰማራው ማህበረሰብ የሚውል ድጋፍ እንደሚያካትት ተጠቁሟል ።

ኢንዶኔዥያ በእስያ-ፓሲፊክ ክልል ከሚገኙ አገሮች ከህንድ እና ቻይና በመቀጠል ሶስተኛዋ ትልቋ የቴክኖሎጂው ተዋናዮች መኖሪያ ናት።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG