በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም የነዳጅ አቅርቦት መስተጓጎል እና የዋጋ ንረት ሥጋት እያየለ ነው


ፎቶ ፋይል፦ የኢራን ባንዲራ ከስቶክ ግራፍ እና የዘይት ፓምፕ
ፎቶ ፋይል፦ የኢራን ባንዲራ ከስቶክ ግራፍ እና የዘይት ፓምፕ

የዓለም የነዳጅ አቅርቦት ሊስተጓጎል እና ከፍተኛ የዋጋ ጭማሬ ሊያስከትል ይችላል የሚለው ሥጋት እያየለ መምጣቱ ተዘገበ።

በመካከለኛው ምሥራቅ የሚታየውን ከፍተኛ ውጥረት ተከትሎ ከኢራን የነዳጅ ኢንዱስትሪ ጋራ በተያያዙ አንዳንድ ተጨማሪ እውነታዎች ሳቢያ ወደ ዓለም ገበያ የነዳጅ ምርት ሊስተጓጎል መቻሉ ተነግሯል።

ከነዳጅ ዘይት ላኪ አገሮች ድርጅት በነዳጅ ምርቷ በሥስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ኢራን በቀን 3 ሚሊዮን በርሜል የሚጠጋ የነዳጅ ዘይት፣ ከጠቅላላው የዓለም የነዳጅ ምርት 3 በመቶ ያህሉን ታመርታለች።

የተከታታይ ዓለም አቀፍ ማዕቀቦች ዒላማ ሆኖ የቆየው የኢራን የነዳጅ ምርት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2015 ከኢራን የኒውክሌር ፕሮግራም ጋር በተያያዘ በምዕራባውያን ኃያላን አገሮች እና በቴህራን መካከል ተደርሶ የነበረው ስምምነት፤ የኢራንን ገቢ ለመገደብ በታለመ ዕቅድ የቀድሞው የዩናይድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ2018 ዳግም ማዕቀቦቹን ተፈጻሚ ካደረጉ በኋላ፣ ኢራን የምታመርተው የነዳጅ መጠን በእጅጉ ቀንሶ መቆየቱ ይታወሳል።

ሆኖም በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የስልጣን ዘመን የማዕቀቦቹን መላላት እና ቻይና ዋናዋ የኢራን ነዳጅ ሸማች እየሆነች መምጣይቷን ተከትሎ ‘ኢራን የማዕቀቦቹን ተጽዕኖ መቋቋም ችላለች’ ሲሉ ተንታኞች ይናገራሉ። በአንጻሩ የባይደን አስተዳደር በኢራን ላይ ጥሎት የነበረውን ማዕቀብ እንዳላነሳ የገለጹት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቤት ቃል አቀባይ በበኩላቸው፣ አስተዳደሩ በቴህራን ላይ የሚያደርገውን ጫና እያሳደገመሆኑን መናገራቸውን ሮይተርስ በዛሬው ዕለት ዘግቧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG