በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮሎምቢያ ከእስራኤል ጋራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን እንደምታቋርጥ አስታወቀች


የኮሎምቢያ ፕሬዚደንት ጉስታቮ ፔትሮ
የኮሎምቢያ ፕሬዚደንት ጉስታቮ ፔትሮ

የኮሎምቢያ ፕሬዚደንት ጉስታቮ ፔትሮ መንግሥታቸው ከእስራኤል ጋራ ያለውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንደሚያቋርጥ ትናንት ረቡዕ አስታወቁ፡፡

ጋዛ ውስጥ በሚካሄደው የእስራኤል ሃማስ ጦርነት ምክንያት ሀገራቸው ከዛሬ ሐሙስ ጀምራ ከእስራኤል ጋራ ያላትን የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንደምታቋርጥ ፕሬዚደንቱ አስታውቀዋል፡፡

ፕሬዚደንቱ ኮሎምቢያ ዋና ከተማ ቦጎታ ላይ ባደረጉት ንግግር የእስራኤልን አመራር “ዘር ለማጥፋት የተነሳ” ብለውታል፡፡ “ የፍልስጥኤም ሞት የሰብአዊነት ሞት ነው ይህ እንዲሆን አንፈቅድም” ብለዋል፡፡

የእስራኤል የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ኢስራኤል ካትዝ ፈጥነው በሰጡት ምላሽ የኮሎምቢያ ፕሬዚደንት ውሳኔ “ለሀማስ ስጦታ ነው” ብለዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ እስራኤል ራፋህ ላይ በምድር ጦር ጥቃት ለመክፈት እየተዘጋጀች ባለችበት ወቅት የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚንስትር ሎይድ ኦስተን ትናንት ረቡዕ የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንትን በስልክ አነጋግረዋቸዋል።

እስራኤል ራፋህ ላይ ምንም ዓይነት ጥቃት ብትከፍት ፍልሥጥኤማውያን ሲቪሎችን ለማስወጣት እና የሰብአዊ ረድዔት አቅርቦት ለማስቀጠል ተዓማኒ ዕቅድ የተካተተበት ሊሆን እንደሚገባ ኦስተን ያሳሰቧቸው መሆኑን የፔንታጎን ቃል አቀባይ ተናግረዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG