በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰው ሕይወት የቀጠፈ ይጠየቃል - ጌታቸው ረዳ፤ የኮምዩኒኬሽንስ ሚኒስትር


ጌታቸው ረዳ፤ የኮምዩኒኬሽንስ ሚኒስትር - ፋይል ፎቶ
ጌታቸው ረዳ፤ የኮምዩኒኬሽንስ ሚኒስትር - ፋይል ፎቶ

“ኦሮሚያ ውስጥ ከተፈጠረው ሁኔታ ጋር ተያይዞ ከታሠሩት ስዎች መካከል ጉዳያቸው ተጣርቶ ወንጀል ያልሠሩ እንደሚፈቱ የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው ረዳ ለቪኦኤ አስታውቀዋል።

“ኦሮሚያ ውስጥ ከተፈጠረው ሁኔታ ጋር ተያይዞ ከታሠሩት ስዎች መካከል ጉዳያቸው ተጣርቶ ወንጀል ያልሠሩ እንደሚፈቱ የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው ረዳ ለቪኦኤ አስታውቀዋል።

ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ቃለ-ምልልስ ያደረገችላቸው የቪኦኤ የአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ክፍል ባልደረባ ጃለኔ ገመዳ “የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ከተሠረዘ የታሠሩት ይፈቱ፤ በመንግሥት ኃይሎች ስለተገደሉት ካሣ ይከፈል” የሚለው ጥያቄ ለምን መልስ አይሰጠውም ስትል ላቀረበችላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ ነው።

የቤተሰቦቻቸው አባላት የተገደሉባቸውና በንብረታቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸውን አስመልክቶም “አላግባብ የሰውን ሕይወት የቀጠፉ ከአንድ ወይም ከሌላ ወገን ያለ፤ ከመንግሥት ወገን ሊሆን ይችላል፤ ያሉ ሰዎች ካሉ በአግባቡ ለሕግ የሚቀርቡበት አሠራር ይፈጠራል፤” ብለዋል ሚኒስትሩ።

“የማስተር ፕላኑን ጥያቄ ተገን አድርገው ሕዝቡን ወዳልተገባ ግጭት የቀሰቀሱ፣ በግልፅ ወንጀል ውስጥ የተሣተፉ ወገኖች ግን ሲጀመርም የእነርሱ ጉዳይ ማስተር ፕላኑ ሳይሆን ሃገር ማተራመስ ስለነበረ ተጠያቂ የሚሆኑበር ሥርዓት ይኖራል” ብለዋል።

በተቃውሞው እንቅስቃሴ ውስጥ ስለመከላከያ ሠራዊቱ ተሣትፎ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው የመከላከያ ሠራዊቱ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ውስጥ ሠፈሮች እንዳሉትና ሁኔታዎች ከፖሊስ አቅም በላይ በሆኑባቸው አካባቢዎች መከላከያ ለእገዛ የተሣተፈባቸው እንቅስቃሴዎች እንደነበሩ ጠቁመው ከዚያ ውጭ ግን የመከላከያ ሠፈሮቹ ከነባር ቦታዎቻቸው ሊወጡ እንደማይችሉ ተናግረዋል።

“የመከላከያ ሠራዊቱ እንደባዕድ ተቆጥሮ ከኦሮምያ ይውጣ የሚባል ጥያቄ አልቀረበም፤ ከውጭ ከሚሰማው በስተቀር” ብለዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ባለፈው ታኅሣስ ስለዚሁ የኦሮምያ አለመረጋጋትና ግጭት ታኅሣስ 6/2008 ዓ.ም ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ውስጥ የተጠቀሙባቸው “ጋኔን” ና “ጠንቋዮች” የሚሉ ቃላት የተደባለቁበት አባባል ኦሮምያ ውስጥ ብዙ ሰው እንዳስቀየመ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ “እኔ ሁከት የጠሩ ወገኖች ነው ያልኩት። ሁከቱን ስለማይመልሱት ሕዝብና መንግሥት ይህንን ሁከት መመለስ ይገባቸዋል፤ በአጋጣሚ የእንግሊዝኛን አባባል ወደ አማርኛ ስመልስ ያስቀየምኩት ሰው እንዳለ ይገባኛል፤ እኔ በታሪኬም፣ በአስተዳደጌም፣ በምወክለው ድርጅትም፣ በምኖርበት ማኅበረሰብም እንኳን የምወድደውን፣ የማከብረውን የኦሮሞ ሕዝብ በዘልማድ እንደጠላት የሚቆጠር የሌላ አካባቢ አገር ወይም መንግሥትንም ቢሆን በእንደዚያ ዓይነት መልኩ የምገልፅ ሰው አይደለሁም፤ ለማንኛውም በአንዳንድ አካባቢዎች ለተፈጠረው ቅሬታ ከልቤ ነው ይቅርታ የምጠይቀው።” ብለዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ፤ የኢትዮጵያ የኮምዩኒኬሽንስ ሚኒስትር ስለኦሮምያ ሁኔታ ዓርብ፤ የካቲት 11/2008 ዓ.ም ከቪኦኤ ጋር ያደረጉትን ቃለ-ምልልስ ከታች የተያያዘውን ማጫወቻ ተጭነው ያዳምጡ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:14:27 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

አቶ ጌታቸው ረዳ፤ የኢትዮጵያ የኮምዩኒኬሽንስ ሚኒስትር ስለኦሮምያ ሁኔታ ታኅሣስ 6/2006 ዓ.ም አዲስ አበባ ላይ ለጋዜጠኞች ሰጥተውት የነበረውን መግለጫ ከታች ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG