በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ነጻነት የሌለባት አገር ተብላለች


 ''ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ነጻነት የሌለባት አገር ናት'' - የፍሪደም ሃውስ (Freedom House) ሪፖርት
''ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ነጻነት የሌለባት አገር ናት'' - የፍሪደም ሃውስ (Freedom House) ሪፖርት

ፍሪደም ሃውስ (Freedom House) መቀመጫውን እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ያደረገና በመናገር ነጻነት ላይ የሚሠራ ዓለም አቀፍ ተቋም ነው፡፡ይህ ተቋም መንግሥታት ለሕዝቦቻቸው የሚሠጡትን የኢንተርኔት ነጻነት አጥንቶ እያንዳንዱ ሀገር ያለበትን ደረጃ ‹‹Freedom on the net 2015 ›› በሚል ርዕስ ስር ሪፖርት አውጥቷል፡፡ በዚህ ሪፖርት ሰንጠረዥ‹‹ኢትዮጵያ ከቻይና፣ከሦሪያ እና ከኢራቅ ቀጥሎ ምንም ዓይነት የኢንተርኔት ነጻነት የሌለባት አገር ተብላለች፡፡

ፍሪደም ሃውስ(Freedom House) የተሰኘው ተቋም "Freedom on the net 2015" የተሰኘው ይህ ሪፖርት በዛሬው ዕለት በቀረበበት ወቅት፤ሪፖርቱን ያዘጋጁት ባለሞያዎች፣የዩኒቨርስቲ መምሕራንንና ተመራማሪዎች፣የጎግል መስሪያ ቤት ባለሞያ፣ከመናገር እና ከመጻፍ ነጻነት ጋር የሚሠሩ ተቋማት ተወካዮች በአጠቃላይ ከሰብዓዊ መብት ጋር የሚሠሩ ግለሰቦችና የድርጅት ተወካዮች ተገኝተው ሪፖርቱን አዳምጠዋል፡፡ ተወያይተዋል፡፡

ማንኛውም ሰው የኢንተርኔት የመረጃ መረብን ተጠቅሞ ያለምንም ቅድመ ምርመራ እና ችግር ሐሳቡን በነጻነት የማስተላለፍ መብት እንዳለው የሚጠቅሰው ይህ ሪፖርት በአሁኑ ወቅት ግን መንግሥታት የሕዝቦቻቸውን የኢንተርኔት ነጻነት እያፈኑ፣አገልግሎቱንም እየዘጉ ከዛ ባለፈ ደግሞ እያሠሩ እንደሚገኙ ይጠቅሳል፡፡

''ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ነጻነት የሌለባት አገር ናት'' -የፍሪደም ሃውስ (Freedom House) ሪፖርት

ኢትዮጵያ የኢንተርኔትም ኾነ የመናገርና መጻፍ ነጻነት ያለባት አገር አይደለችም

አገራት ለሕዝቦቻቸው የሚሰጡትን ነጻነት በሦስት ቀለማት ከፍሎ ያስቀመጠው የሪፖርቱ አንድ አካል የኾነው አንድ ሠንጠረዥ ኢትዮጵያ ከቻይና፣ከሦሪያ እና ከኢራቅ ቀጥሎ "የባሰ አፈና" ባለባቸው አገራት ዝርዝር ውስጥ ያስቀምጣታል፡፡ በሌላኛው የሪፖርቱ ክፍል ደግሞ "ኢትዮጵያ የኢንተርኔትም ኾነ የመናገርና መጻፍ ነጻነት ያለባት አገር አይደለችም" ይላታል፡፡

እአአ የ2015 ፍሪደም ሃውስ (Freedom House) ሪፖርት የአገራት ኢንተርነት ነጻነትን የሚያሳይ ካርታ

በዛሬው ዕለት በ "ጉግል" መሥሪያ ቤት የቀረበውን ሪፖርቱን ያዘጋጀው ፍሪደም ሃውስ፤የአፍሪካ አገሮች ሲኒየር ፕሮግራም ኦፊሰርና ሪሰርች አናሊስት ማይ ትራንግን አነጋግራ ጽዮን ግርማ ያጠናከረችውን ዘገባ ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡

ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ነጻነት የሌለባት አገር ተብላለች
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:46 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG