በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የውጪ ዜጎች በመኖሪያ ቤት ግንባታና ችርቻሮ መስክ መሳተፍ እንዲችሉ ሕግ በመረቀቅ ላይ ነው


ፎቶ ፋይል፦ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
ፎቶ ፋይል፦ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

በኢትዮጵያ የውጪ አገራት ዜጎች በመኖሪያ ቤት ግንባታ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በችርቻሮ ንግድ መስክ መሳተፍ እንዲችሉ መንግሥታቸው ሕጋዊ ሁኔታዎችን እንደሚያመቻች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሣምንቱ መጨረሻ አስታውቀዋል።

“የውጪ አገራት ዜጎች የቤት ንብረት ባለቤት እንዲሆኑ የሚያስችል ሕግ እናወጣለን” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከንግድ ማኅበረሰብ አባላት ጋራ ባደረጉት ስብሰባ ላይ መናገራቸውን የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ካሰራጩት ዘገባ መረዳት ተችሏል።

ሕጉን የማርቀቁ ሂደት የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

በተጨማሪም መንግሥት በችርቻሮ ንግድ ዘርፍ ያለውን ገደብ በማላላት ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆኑ የውጪ አገራት ኩባንያዎችም እንዲሳተፉ እንደሚደረግ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስታወቃቸውን የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG