በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለኢሕአዴግ ጥፋት መነሻው፣ ሕዝብ ያሰማው ቅሬታ አይደለም ተባለ


ፋይል ፎቶ - የአረና ትግራይ ፓርቲና የመድረክ የአመራር አባል አቶ ገብሩ አሥራት
ፋይል ፎቶ - የአረና ትግራይ ፓርቲና የመድረክ የአመራር አባል አቶ ገብሩ አሥራት

የአረና ትግራይ ፓርቲና የመድረክ የአመራር አባል አቶ ገብሩ አሥራት ከሌሎች ሁለት የፖለቲካ ተንታኞች ጋር፣ በጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሪፖርት ላይ በመጽሔቱ ክፍል ትንታኔ ይሰጣሉ።

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ባለፈው ሐሙስ ለፓርልማቸው ባቀረቡት ሪፖርት፣"በኦሮሚያና በሌሎችም አካባቢዎች ለተፈጠረው የሕዝብ ቅሬታ ፓርቲዬና መንግሥቴ ኃላፊ ናቸው" ብለዋል። ምን ማለትነው? "ኃላፊነት መውሰድ" ሲባልስ እስከምን ድረስ ይሄዳል?

በዚህና በሌሎችም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት ላይ ሦስት እንግዶችን ለትንታኔ ጋብዘናል።

ሁለቱ ከኢትዮጵያ ናቸው፤ አቶ ገብሩ አሥራት፣ የአረና ትግራይ ፓርቲና የመድረክ አመራር አባል፣ አቶ አበባው አያሌው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና የሥነ-ጥበብ መምህር፣ ከዚህ ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሮፌሰር ዓለማየጉሁ ገብረማራም በካሊፎርንያ ስቴት ዩኒቨርስቲ (California State University) የፖለቲካ ሳይንስና የህገ-መንግሥት መምህር።

ያወያያቸው አዲሱ አበበ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ሪፖርት አንድ ዘለላ ነቅሶ በማውጣት ይጀምራል። ውይይቱን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።

ለኢሕአዴግ ጥፋት መነሻው፣ ሕዝብ ያሰማው ቅሬታ አይደለም ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:03 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG