በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አጎዋ ካልታደሰ በሚቀጥለው ዓመት ያበቃል - ሴነተሮች እንዲታደስ ጠይቀዋል


ፎቶ ፋይል፦ ሴነተር ክሪስ ኩንስ
ፎቶ ፋይል፦ ሴነተር ክሪስ ኩንስ

የዩናይትድ ስቴትስ ሴኔተሮች ክሪስ ኩንስ እና ጄምስ ሪሽ እአአ የ2024 የአፍሪካ የእድገት እድል ድንጋጌ (አጎዋ) ህግ የሚያድሰውን እና የሚያጠናክረውን ህግ ዛሬ አቅርበዋል፡፡

ህጉ በአሜሪካ እና ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት መካከል ቁልፍ የንግድ ልውውጥ እንዲኖር የተደነገገውን አጎዋን ለማደስ ያለመ ነው።

እአአ በ2000 የወጣው የአጎዋ ህግ በዩናይትድ ስቴትስ እና ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት መካከል ጥልቅ ኢንቨስትመንት እና ጠንካራ የንግድ ግንኙነትን የሚያመቻች መርሃ ግብር ነው።

ሴኔተሮቹ ያቀረቡት የአጎዋ እድሳት እና ማሻሻያ ህግ በህግ መወሰኛው ዴሞክራትና ሪፐብሊካን ምክር ቤት አባላት ድጋፍ የተረቀቀ ነው፡፡

ህጉ ዲሞክራቶቹ የኮሎራዶ ሴነተር ማይክል ቤኔት፣ የኢሊኖዩ ዲክ ደርበን እና የሚሪላንዱ ክሪስ ቫን ሆለን ከሪፐብሊካኖች በኩል ደግሞ በደቡብ ዳኮታው ሴኔተር ማይክ ራውን እንዲሁም በኢንዲያው ቶድ ያንግ ድጋፍ መቅረቡ ታውቋል፡፡

የቀረበው ህግ የእድሳት እና ማጠናከሪያ ህግ የአፍሪካን የእድገት እድል ድንጋጌን (አጎዋን) እአአ እስከ 2041 ድረስ ያራዝመዋል። ይህ የረዥም ጊዜ ማራዘሚያ፣ የአቅርቦት ሰንሰለቱን ከቻይና ውጭ ማስፋት ለሚፈልጉ በርካታ የንግድ ተቋማት ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት መዋዕለ ንዋያቸውን ለማሳደግ የሚያስፈልጋቸውን ዋስትና ይሰጣል።

ከዓለም ከየትኛውም አካባቢ የሚበልጥ ቁጥር ያለው ወጣት eና ብዙ አዳጊ ኢኮኖሚዎች ባሉት በዚህ የአፍሪካ ክፍል አጎዋ ኢኮኖሚ ልማት ጥንካሬ ወሳኝ አስተዋጽኦ ከማበርከቱም ሌላ አሜሪካም በቀጠናው ያላትን የኢኮኖሚ ተሳትፎ አጠናክሯል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG