በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ሀገራችን ላይ እየኖርን አይመስለኝም” ከታክሲ አሽከርካሪዎች አንዱ


“ሁላችንም የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ነን።ሕጉ ተግባራዊ የሚደረግ ከሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ ክሥራ ውጪ እንሆናለን።’’ በዛሬው ዕለት የታክሲ ማቆም አድማ ካደረጉት የታክሲ አሽከርካሪዎች በከፊል፡፡

በአዲስ አበባ የመንገድ ትራፊክ ደኅንነት ደንብን ለማስከበር ከአምስት ዓመት በፊት የወጣውና በከፊል ሲተገበር የነበረው ሕግ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ በመጀመሩ የአዲስ አበባ ታክሲ አሽከርካሪዎች በሙሉ በዛሬው ዕለት ሥራ የማቆም አድማ መተው ውለዋል፡፡

ፌደራሉ የትራንስፖርት ባለሥልጣን ትናንት ባወጣው መግለጫ ትግበራው ለሦስት ወር መራዘሙን አስታውቋል፡፡አሽከርካሪዎቹ ደግሞ “ለሦስት ወር ማራዘም መፍትኄ አይደለም ዘላቂ መፍትሄ እንፈልጋለን” ይላሉ፡፡

በአዲስ አበባ ካሳንቺስ አካባቢ ታክሲ ያጡ ተሳፋሪዎች ለጊዜው በተመድቡ አውቶብሶች ላይ ለመሳፈር ሰልፍ ይዘው፡፡
በአዲስ አበባ ካሳንቺስ አካባቢ ታክሲ ያጡ ተሳፋሪዎች ለጊዜው በተመድቡ አውቶብሶች ላይ ለመሳፈር ሰልፍ ይዘው፡፡

አሽከርካሪዎችን የአዲስ አበባን ፖሊስ ኮሚሽንን ያነጋገረችው ጽዮን ግርማ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡

“ሀገራችን ላይ እየኖርን አይመስለኝም” ከታክሲ አሽከርካሪዎች አንዱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:45 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG