በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ ለማዛወር እንግሊዝ የነደፈችው ረቂቅ ሕግ ሊጸድቅ ነው


የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ
የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ

ብሪታንያ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ ለማዛወር የያዘችው እና ከፍ ያለ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር የታመነው ዕቅድ የሃገሪቱ ሕግ ሊሆን ተቃርቧል። የዕቅዱ ተቃዋሚዎች በአንጻሩ ስደተኞቹን በኃይል ከአገር የማስወጣቱን ውጥን ማገድ የሚችል አዲስ የሕግ መቋቋሚያ ለማበጀት ጥረት ይዘዋል።

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን እገዳ ተጽዕኖ ለማስቀረት እና በላይኛው ምክር የቀረበውን ተቃውሞ ለመቋቋም የታለመው ይህ ሕግ በያዝነው ሳምንት በሃገሪቱ ፓርላማ ይድቃል ተብሎ ተጠብቋል።

‘የሩዋንዳ ዕቅድ’ የሚል ቅጽል የተሰጠው ይህ ውጥን ጠቅላይ ሚንስትር ሪሺ ሱናክ ‘ሕገ ወጥ ስደተኞችን ወደዚያች አገር የሚያጓጉዙ ጀልባዎች እንቅስቃሴ’ ለማስቆም ለገቡት ቃል ‘ወሳኝ እርምጃ ነው’ ተብሏል።

ጉዳዩን አመልክቶ አስተያየት የሰጡት የሱናክ ቃል አቀባይ ዴቭ ፓሬስ ትናንት ሲናገሩ "የእንግሊዝ ፓርላማ በያዝነው ሳምንት በሕገ ወጥ አስተላላፊዎች ከፍተኛ እንግልት እና ብዝበዛ የሚፈጽምባቸውን ሰዎች ህይወት የሚታደግ ህግ የማጽደቅ እድል ያገኛል" ብለዋል ። “አሁን ባለው አካሄድ መቀጠል እንደማንችል ግልፅ ነው። በመሆኑም ይህ ሁኔታ የሚለወጥበት ጊዜው አሁን ነው” ሲሉም አክለዋል።

በአነስተኛ ጀልባዎች ተጓጉዘው የእንግሊዝ ቻናልን በማቋረጥ ከዚያ የሚደርሱትን ጥገኝ ነት ጠያቂዎች ወደ ምሥራቅ አፍሪካዊቱ አገር ለማዛወር እና በቋሚነትም ኑሯቸውን ከዚያ እንዲያደርጉ በማቀድ ሁለቱ አገሮች የተፈራረሙት ስምምነት ሁለት ዓመታት አስቆጥሯል። በፍርድ ቤት የታገደው ዕቅድ እንግሊዝን በትንሹ 470 ሚሊዮን ዶላር ሊያስወጣት እንደሚችልም ተገምቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG