በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢራን እስራኤልን ለመበቀል ዛተች


በሶሪያ የሚገኘው የኢራን ቆንሱላ በእስራኤል የአየር ጥቃት ተፈጽሞበት
በሶሪያ የሚገኘው የኢራን ቆንሱላ በእስራኤል የአየር ጥቃት ተፈጽሞበት

እስራኤል በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ በሶሪያ በሚገኘው የኢራን ቆንስላ ላይ በፈጸመችው ጥቃት፤ ሁለት የኢራን ከፍተኛ የጦር ጄኔራሎችን ጨምሮ 12 ሰዎች የሞቱ ሲሆን፤ ይህን ተከትሎ አንድ ከፍተኛ የኢራን ባለስልጣን ‘ኢራን ትበቀላለች’ ሲሉ ዝተዋል።

ጄኔራል ሞሃመድ ባግሀሪ ጄኔራል ሞሃመድ ረዛ ዛሂዲን ለመቅበር ለተሰበሰቡት ለቀስተኞች ኢራን መቼ የበቀል ተልዕኮዋን እንደምትፈጽም እና እንዴት እንደምታቀነባብረው ታስብበታለች ሲሉ ተናግረዋል። “ጊዜው፣ የጥቃት ዓይነቱ እና ተልዕኮው እስራኤል በፈጸመችው ድርጊት እንድጸጸት ሆኖ እንዲፈጸም እኛ እንወስናለን” ብለዋል ጄነራሉ።

ያህያ ራሂሚ ሳፋቪ የተሰኙ የአያቶላ አሊ ካሃሚኒ አማካሪ ባለስልጣን ደግሞ የኢራን የዐብዮት ዘብ አባላትን ከገደለው የሶሪያው ጥቃት በተመለከተ ኢስና ከተሰኘ የዜና አውታር ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ከዚህ በኋላ የእስራኤል ኤምባሲዎች ደህንነታቸው የተጠበቁ አይሆንም ብለዋል። ባለስልጣኑ ባደረጉት ንግግር “ከዚህ በኋላ የጽዮናዊያን አገዛዝ ኤምባሲዎች ደህንነታቸው የተጠበቁ ስፍራዎች አይደሉም” ነው ያሉት።

እስራኤል በኢራን የዲፕሎማሲ ማረፊያ ላይ የፈጸመችው ጥቃት በሁለቱ ባላንጣ ሀገራት መካከል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው ውጥረት ማሳያ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG