በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪቃ በጋዜጦች


አፍሪቃ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን፣ ስለ አፍሪቃ ከተጻፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል። ኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ 15 እስከ ሀያ ዘማናዊ ቦይንግ አይሮፕላኖችን እንድሚገዛ አስታወቀ፣ በኢትዮጵያ የሚመሰረተው የኩላሊት ነቅሎ ተከላ ማዕከል በሀገሪቱ ያለውን የህክምና ይዘት እንደሚለውጥ ተገለጽ፣ አንዲት ቻይናዊት ነጋዴ አፍሪቃ ውስጥ በድብቅ የዝሆን ጥርስ አሰጛጛሪነት ወንጀል ታያዙ የሚሉትን ርእሶች ነው በዛሬው ዝግጅታችን የምንመለከተው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ 15 እስከ 20 ቦይንግ 777x የረጅም ርቀት ቦይንግ አውሮፕላኖችን የመግዛት ትእዛዝ እስከ ታህሳስ ወር ባለው ጊዜ እንደሚያቀርብ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ እንደገለጹ ዋል ስትሪት ጆርናል (The Wall Street Journa) ድረ-ገጽ ዘግቧል። ቦይንግ 777x የቦይንግ አዲሶቹ አውሮፕላኖች ናቸው።

SE A350-1000 widebody የአየር ባስ አውሮፕላኖችን የመግዛት እቅድ እንዳለም የአየር-መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ገልጸዋል። የሚከፈለው ዋጋም $7.4 ቢልዮን ዶላር እንደሚሆን ድረ-ገጹ ጠቁሟል።

እስከ መጪው ታህሳስ ወር ባለው ጊዜ ውስጥ የሚታዘዙት ዘማናዊ ጀት አውሮፕላኖች ከ 2020 አም በኋላ (ከአምስት ዓመታት) በኋላ ማለት ነው ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ቆየት ያሉትን አስር 777 የጥንድ ሞተር አውሮፕላኖችን እንደሚተኩ አቶ ተወልደ ገልጸዋል።

የሚችጋን ዩኒቨርሲቲ አዲስ አበባ ከሚገኘው የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚለንየም የህክምና ኮሌጅ ጋር በመተባበር፣ ኢትዮጵያውያን ሀኪሞችን በቀዶ ህክምና ጥበበ እንደሚያሰለጥን፣ ሚችጋን ዴይሊ (The Michigan daily) ጋዜጣ ድረ-ገጽ ገልጿል።

የሚችጋንና የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ባደርጉት ትብብር ምክንያት፣ ሶስት ሊሞቱ ይችሉ የነበሩት የኩላሊት በሽተኞችን በቅርቡ በነቅሎ ተከላ ህክምና ምክንያት ህይወታቸው እንደተርፈ ተዘግቦ እንደነበር ይታወሳል።

አሁን ሁለቱ የህክምና ትምህርት ቤቶች የሚያተኩሩት፣ የኩላሊት ነቅሎ ተከላ ማዕከል በመገንባት ላይ ሲሆን፣ ፕሮግራሙ በሞያው ልዩ ጥበበ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ሀኪሞች ማሰልጠንን በሆስፒታሉ ያሉት የላብራቶሪ ማሳለጫዎችንና በጽኑ የታመሙ በሽተኞች የሚታከሙበት አገልግሎት ማሻሻልን የመሳሰሉ መርሀ-ግብሮች እንደሚካተቱባት፣ በቅዱስ ጳውሎስ የተደረገው መሻሻልም፣ በሀገሪቱ ዙርያ ወዳሉት ሆስፒታሎች እንደሚስፋፋ፣ ሚሽጋን ዴይሊ (The Michigan daily) ጋዜጣ ድረ-ገጽ ጠቅሷል። ሌሎች ርእሶች በአፍሪቃ በጋዜጦች ፕሮግራም ላይ አዳነች ፍሰሀየ አቀናብራ አዘጋጅታለች። ሙሉውን ዝግጅት የተያያዘውን የድምጽ ፋይል በመጫን ያድምጡ።

አፍሪቃ በጋዜጦች /ርዝመት - 10ደ06ሰ/
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:05 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG